Ethiopian language Viewpoint

ክቡር ዐቢይ፤ እባክዎን ስልጣንዎን በፍቃድዎ ይልቀቁ፤ እንደእርስዎ ኢትዮጵያዊ ወንጌላዊ ከሆነ ሰው የቀረበ ጥሪ

ከአገራችን ሰላም በላይ የራስዎን ስልጣን አስቀድመዋል ስለዚህ አሁን ከስልጣን ሊወርዱ የሚገባበት ጊዜ ነው

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሊ (PhD)

ደብዳቤዬን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላምታ በመስጠት ልጀምር እወዳለሁ።

እኔ ናዖል በፍቃዱ እባላለሁ፤በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቀደምት  መጥምቃውያን ሥነ-መለኮት ኮሌጆች ውስጥ አንዱ በሆነው ኮሌጅ መምህርና በ ክርስቲያናዊ አመራር ትምህርት የ PhD እጩ ነኝ። ይህንን ደብዳቤ ለመፃፍ የተነሳሳሁት በራሴ ክርቲያናዊ ሥነ-ምግባር መርሆዎች ላይ ተመርኩዤና ባለፉት አመታት የአመራራ ዘዴዎችዎን ከተከታተልኩ በኋላ ልቤን ስለከበደኝ/ከፍተኛ ኃላፊነት ስለተሰማኝ ነው። ስለዚህ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ እንደእርስዎ ወንጌላዊ እንደሆነ ወንድምና የሥነ-መለኮት መምህር እንደመሆኔ ጽፌሎታለሁ። 

በሚገባ እንደሚያውቁት ሥነ-መለኮት በእግዚአብሔር አስተምህሮ ላይ የሚደረግ ጥናት ነው። የክርስቲያን ሥነ-መለኮት መጽሐፍ ቅዱስን በእግዚአብሔር ባሕርያት ላይ በሚደረግ ጥናት ላይ ከሁሉም የላቀ ስልጣን ያለው ነው ይላል።  

የሥነ-መለኮት መምህር ተግባር አስተምህሮዎችን መፈተሽ ብቻ ሳይሆን የሥነ-መለኮት ትምህርትን ከአንድ ህብረተሰብ ዘመናዊ ሁኔታዎች ጋር በማግባባት/በህብረተሰቡ አውድ በመቃኘት ከዕለት ተዕለት ህይወት ጋር የሚጣጣምና የሚተገበር ማድረግ ነው። ይህ አንዳንድ ጊዜም የማህበረሰብ ሥነ-መለኮት (Public Theology) በመባል ይጠራል። ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የወንጌል ሚኒስትር፣የዓለም ሚሽን ተማሪ እንዲሁም የሥነ-መለኮት መምህር ሆኜ በነበርኩባቸው በአብዛኛው ጊዜያት ለማድረግ ስሞክር የነበረው ይህን ነው። 

ዛሬ ደብዳቤዬን የማቀርብሎት በአገራችን እጣ ፋንታና የእርስዎ አመራር በተጫወተው አጥፊ ሚና ከባድ ሀዘን እየተሰማኝ ነው። 

አድናቆት በተቸረው ሁኔታ ወደ ስልጣን መውጣት

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች በመጋቢት 24 2010 ዓ.ም ስለተፈጠረው ነገር ሕያው ትውስታ አላቸው። የደስ ደስ ያለው ወንጌላዊ ፓለቲከኛ የጠቅላይ ሚኒስትር ስፍራው (ቦታው/ስልጣን) ላይ በተሰየመ ጊዜ በአይናችን ተዓምር ሲሰራ ተመለከትን። ቤተክርስቲያናት እንዲሁም መስጊዶች በደስታ ዝማሬዎች ተሞልተው ነበር። ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የእርስዎ ወደ ስልጣን መምጣት ህዝቡን ለጎበኘው ለሃያሉ እግዚአብሔር ክብር እንዲሰጥ ነው ያደረገው/ህዝቡን የጎበኘው የሃያሉ እግዚአብሔር ክብር እንዲገለጥ ነው ያደረገው?

ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ እንዲሁም በአገሪቱ በሙሉ በነበሩ ተቃውሞዎች ‘’ኢየሱስ የማያደርገው ምንድነው?’’ (በወቅቱ የነበረውን የአገሪቱን ሁኔታ የሚመለከት ነው) የሚል ርዕስ ያለው የአማርኛ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፤ በጽሁፉም ሁሉም ክርስቲያኖች በአገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ እንዲሆኑና አለመግባባቶችን በአመጽ ለመፍታት ከመሞከር እንዲቆጠቡ/እንዲርቁ ጠይቄያለሁ። 

እርስዎ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የማሻሻያ ስራዎችን እየተገበሩ በነበረ ወቅት እኔ The Economist ላይ ቶም ጋርድነር የእርስዎን አስተዳደር የPentecostal-charismatic (ይህ የክርስትና አይነት የመንፈስ ቅዱስን፣የመንፈሳዊ ስጦታንና የአሁን ዘመን ተዓምራትን የአንድ አማኝ የሁልጊዜ ህይወት አካል አድርጎ የሚያጎላ ነው) ያለው እንደሆነ አድርጎ ለጻፈው ጽሁፍ ምላሽ ‘’የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ሥነ-መለኮት ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል ወይ? ‘’የሚል ርዕስ ያለው አስተዳደርዎን የሚያደንቅ ጽሁፍ ጽፌያለሁ። በክርስትና መርሆችዎ የተነሳ አስተዳደርዎ ወደ ፓለቲካ ጠረጴዛው ያመጣቸውን እሴቶች አቅርቤያለሁ። የእርስዎ ወደ ስልጣን መምጣት በአገሪቱ በርካታ ታሪካችን መሳደድ ለነበረበት ለኛ ለፕሮቴስታንቶች በሙሉ የሚያኮራ ነበር።  

ወደ ስልጣን ከመጡ ከአንድ አመት በኋላ ‘’የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 365 ቀናት በስልጣን ላይ፡ ክርስትያናዊ ምልከታ’’ የሚል ሌላ ጽሁፍ ከትቤያለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ባገለገሉበት የመጀመሪያው ዓመት ያሳኩትን ነገሮች አድንቄያለው እንዲሁም በወንጌላዊ ክርስቲያን ምልከታ አማካይነት ልገልጻቸው ሞክሬያለሁ። እስረኞችን ለመልቀቅ የወሰኑትን ውሳኔ፣ከኤርትራ ጋር ያወረዱትን እርቅ እና ሁለቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ሲኖዶስ አንድ  ማድረግዎን አድንቄያለሁ። 

የማህበረሰብ የሥነ-መለኮት መምህር ተግባሩ ለህብረተሰቡ ተገቢ የሆኑ የሥነ-ምግባር መርሆዎችን ማጉላት እንደመሆኑ አገሪቱን አንድ ለማድረግ የተጠቀሙበት የሥነ-ምግባር ማዕቀፎች ላይ በመመስረት እንቅስቃሴዎችዎን አንድቄያለሁ። ያ የእውነት የሚያስደንቅና የማይረሳ ነው። 

ሌላኛው ገጽታ

ምንም እንኳን የሥነ-ምግባር አመራርዎን ያደነቅኩ ቢሆንም የተወሰኑ አካሄዶችዎ በእርስዎ በኩል የተሳሳቱ እርምጃዎች ይፈጠራሉ ብዬ እንድገምት አድርገውኛል። በ2011 ዓ.ም ለማስተርስ ዲግሪዬ ባዘጋጀሁት ጽሁፍ ስለcharismatic leadership (የደስ ደስን፣የግል ግንኙነትንና ሌሎችን ለማነሳሳት አሳማኝ የእርስ በእርስ ግንኙነት ጥቅም ላይ የሚያውል አየመራር ዘዴ ማለት ነው) አደገኛ ጎኖች ጽፌ ነበር (ጽሁፉ በከፊል በእርስዎ አመራር ምክንያት የተጻፈ ነው)። ህዝባዊ እርምጃዎችዎ የተጋነነ አድናቆት ከማቅረቤ በፊት ቆም ብዬ እንደገና እንዳስብ አደረጉኝ። 

እነዚህ ጥርጣሬ የሚያጭሩ እርምጃዎች የእርስዎን ርዕዮተ ዓለም ብቻ በሚቀበሉ ሰዎች እራስዎን መክበብ ከጀመሩ በኋላ የበለጠ ግልጽ እየሆኑ መጡ። እንደ ዶክተር ለማ መገርሳ ያሉ ተፎካካሪ የፓለቲካ ሰዎች ገሸሽ ተደረጉ። በዛን ጊዜያት እራሱ እምነቴ የእርስዎ አስተዳደርን እንድደግፍ አሳምኖኝ ነበር ምክንያቱም የፍቅርና አንድነት ስብከቶችዎ ከእርምጃዎችዎ ጋር ተቃርነው አያውቁም ነበር። ምንም እንኳን ጉድለቶች ቢኖሩም በአብዛኛው የሚናገሩትን ይተገብሩ ነበር። 

ጊዜ እየሄደ ሲመጣ ኢትዮጵያዊ ወንጌላውያን በህግ የተደነገገ አካል ሆነው እውቅና ለማግኘት እንዲችሉ አንድነት እንዲፈጥሩ ጫና በማድረግ ለወንጌላውያን ትልቅ ስጦታ አበርክተዋል። ይህን እንቅስቃሴ የፕሮቴስታንት ሥነ-መለኮት ሊቆችንና የክርስትና እምነትን የከፋፈለውን ቫይረስ መዋጊያ መንገድ በማድረግ ደግፌው ነበር። ይህንን ሐሳብ ከመደገፍ ባለፈ ክርስቲያናዊ አድንነት የዚህን ህዝብ እጣ ፈንታ እራሱ ለማትረፍ እንደሚችል ጠቁሜ ነበር። ‘’ክርስቲያናዊ አንድነት ኢትዮጵያን ሊያድን ይችላል?’’ የሚለው ጽሁፌ ላይ የእርስዎን የመደመረ ፍልስፍና በመከተል ቤተክርስቲያናት ታላቅ አንድነት እንዲመሰርቱ ተሟግቼያለሁ። 

ነገር ግን የሥነ-መለኮት  መምህራን የሆኑ ጓደኞቼ ‘’ዐቢይ ፓለቲካ እየተጫወተ ነው’’ በማለት ተቹኝ። 

አልሰማኋቸውም። 

የነገሮች መለዋወጥና ተማጽኖ 

በእንደዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ነገሮች እንደዚህ ይለዋወጣሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር። በአስተዳደርዎ ሁለተኛ ዓመት እንደ ሥነ-መለኮት መምህርነቴ ለእርስዎ እንድሟገት ያደረጉኝ መጀመሪያ ላይ ያየኋቸው እሴቶች መደብዘዝ ጀመሩ በምትኩም ሌላ ገጸ-ባህሪ (ይህን ጊዜ ደግሞ መሰሪ/ተንኮለኛ) የሆነ ገጸ-ባህሪ ብቅ አለ። ፍቅር አሁንም በከንፈርዎት ላይ ነበር ነገር ግን ድርጊቶችዎ የበለጠ ከራስ ውጪ ለመመልከት ባለመቻል (በራስ ላይ በማተኮር) የተነሳ የሚደረጉ ነበሩ። 

ሁሉም እርስዎ ሲሏቸው የነበሩ ነገሮች በተቃራኒ ድርጊቶች ሲተኩ ሲሰብኩ የነበሩትን ነገሮችን በሙሉ እውነተኛነታቸውን መጠራጠር ጀመርኩ። በፓለቲካዊ ቋንቋ ለመናገር፤እራስ ላይ የሚያተኩር፣ሁለት መልክ ያለው መሪ ምሳሌ ሆኑ። ለአንድ ዓመት ተኩል ባለማመን በዝምታ ቆየሁ። 

ሁሉንም ንግግሮችዎንና እርምጃዎችንዎ ከተከታተልኩ እንዲሁም በፀሎት ካሰብኩበት በኋላ አዕምሮዬን ቀይሬያለሁ እናም አስተዳደርዎን ማውገዝ አለብኝ። በሥነ-ምግባር ብቁ ያልሆኑና 110 ሚሊየን ህዝብ መሪ ለመሆን በቂ ችሎታ የሌለዎት ሆነው አግኝቼዎታለሁ። ስለዚህ እርስዎን መተቸት ሥነ-ምግባራዊና ሥነ-መለኮታዊ ግዴታዬ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሁን እርስዎ ከስልጣንዎ እንዲለቁ እየጠየኩ ነው።

ከስር እዚህ ድምዳሜ ላይ እንድደርስ ያደረጉኝን 6 ምክንያቶች እገልጻለሁ። 

1. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ካውንስል በፓለቲካ ውስጥ ጣልቃ መግባት  

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሁሉም እርምጃዎችዎ አብልጬ የደገፍኩት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ካውንስል ምስረታን ነበር። ምንም እንኳን በርካታ ብልህ ሰዎች ተዓቅቦ እንዳላቸው ቢናገሩም ይህንን እንቅስቃሴ ደግፌ ነበር ምክንያቱም ካውንስልው በወንጌላውያን መካከል ባለው የሥነ-መለኮት መረዳትና ውይይት ብቻ ሳይሆን በብሔራዊ አንድነት ላይ በሚጫወተው ሚና ስላመንኩ ነበር። ‘የተከፋፈለች ቤተክርስቲያን የተከፋፈለች አገርን አንድ ማድረግ አትችልም’ በሚለው የድሮው መርህ አምናለሁ። 

በጊዜ ብዛት ግን የካውንስልው ተግባር ሊገመት የማይችል/ከምገምተው ውጭ ነው የሆነብኝ። የካውንስልው መሪ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ በይፋ እራሳቸውን እንደ ብልጽግና ፓርቲ አባልና እጩ አቀረቡ። እስከአሁን ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ከፍተኛ ወንጌላዊ አካል እየመራ የሚገኘው የፓለቲካ ሰው ነው። 

ምንም እንኳን ክርስቲያን በፓለቲካ ጉዳዮች ውስጥ መሳተፉ ከእምነት ስርዓታችን ጋር የሚቃረን ባይሆንም የቤተክርስቲያን መሪ ግን በፓለቲካ ውስጥ ወገንተኛ ከመሆን መቆጠብ አለበት። የተወሰኑ ሙስሊሞችና የኦርቶዶክስ መሪዎች በብሔራዊ ምርጫ ውስጥ ቢሳተፉም እንኳን አብዛኞቹ (የእርስዎ አማካሪን ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ) ከማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ ሆነው ቆይተዋል። 

ነገር ግን የወንጌላዊው ካውንስል መሪ አዲስ የተመሰረተውን የእርስዎን ብልጽግና ፓርቲ በመቀላቀል ከእርስዎ ጋር ወግኗል። የዚህ ውሳኔ አንድምታ እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ይህን ዜና በሰማሁኝ ቅጽበት የካውንስሉ ፕሬዝደንት ከስልጣን እንዲለቁ ከጠየቁ የቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል አንዱ ነበርኩ። በመጨረሻም ምንም ምላሽ አልነበረም። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስታዊ ሃይማኖት እንዳይፈጠርና የመንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ውስጥ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር ለማድረግ ቤተክርስቲያንና መንግስት የመለያየታችውን አስፈላጊነት ጠንቅቀው ይረዳሉ። መንግስታዊ ሃይማኖት  በ1967 ዓ.ም በመንግስት ገለልተኝነት የተተካ ሲሆን በሃይማኖት ውስጥ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ግን በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ብቅ ብሏል። 

የቤተክርስቲያን መሪዎች በመንግስት እንዳይናገሩ ተደርገዋል እንዲሁም የነብይነት ድምጻቸውን የባለስልጣናትን የስነምግባር ጉድለቶች ለመጠቆም እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል። ይህንን በእርስዎ አስተዳደር በገዛ አይኔ አይቻለሁ። ካውንስልው በእርስዎ የፓለቲካ እምነትና የፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ጣልቃ ገብነትና ቁጥጥር እጅግ ያለበት በመሆኑ እርስዎን መተቸት ፀረ-ፕሮቴስታንት አቋም መያዝ እንደሆነ ተደርጎ መታየት ጀምሯል። 

በአምባገነኑ ደርግ ላይ በነበራቸው ትንቢታዊ ድምጽ የተነሳ ህይወታቸውን መስዋዕት ያደረጉ እንደ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ያሉ ሰዎች ባሉበት አገር አሁን ቤተክርስቲያን የአንድ ፓለቲከኛ ርዕዮተ-ዓለም ባሪያ ሆናለች። የፈለጉት ሰው እንዲገደል ቢያዙ ማንም የሃማኖት መሪ አይቃወምዎትም። 

በዚህም የተነሳ በምድር ላይ የእግዚአብሔር አፍ የሆነችውን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ዝም በማሰኘትና በመቆጣጠር ተሳክቶሎታል።  ቤተክርስቲያንን ድምጽ ለሌላችውና ለተጨቆኑ ድምጽ ከመሆን በእርስዎ ስብዕና የሚመራው አስተዳደር የድምጽ ማጉያ ወደ መሆን ቀይረዋታል። የአሁን ‘ነቢዮች’ አባላቶቻቸውን እርስዎን በመጥቀስ ‘በእግዚአብሔር የተቀባ’ን ሰው እንዳይናገሩ ያስጠነቅቃሉ። የእርስዎ ባልደረባ እንደሆኑ የሚናገሩ መጋቢዎች በመድረኮቻቸው እርስዎ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ ከእግዚአብሔር የተላኩ መሲሕ እንደሆኑ በይፋ ያውጃሉ። 

የቤተክርስቲያን መሪዎች የእርስዎን ማንኛውንም ተግባር አይተቹም/አይኮንኑም። የአመራር ስነ-ምግባር ጉድለትዎን አይተቹም። በህዝባዊነትዎና በካውንስሉ ውስጥ ጣልቃ ገብነት በመኖሩ የተነሳ ዝም እንዲሉ ተደርገዋል። ግፋ ሲልም በፕሮቴስታንት የሚመራ ምድራዊ መሲሃዊ መንግስት እየጠበቁና ለዛም ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። ቤተክርስቲያን ባህላዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባሮቿን ወደ ጎን በማለት የእርስዎን ንግግሮች በማስተጋባት ተጠምዳለች። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ተከታዮችዎ ለእርስዎ አምባገነናዊ ሃሳቦችና በስልጣን ግፊት ለሚካሄድ እንቅስቃሴዎችዎ እውቅና ቢሰጡም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግን ለማንኛውም የ Protestant-imperialist (ፕሮቴስታንታዊ የቅኝ ቅዛት አስተሳሰብ) ፍላጎት ሊንበረከክ አይችልም። ወንጌላውያን ለእርስዎ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እቅድ የሚማገዱ ማገዶዎች አይደሉም። የእርስዎ የፓለቲካ ምኞት ወኪሎች አንሆንም። 

የእርስዎ ስልጣን ላይ መሆን ቤተክርስቲያንን አልጠቀመም በምትኩ ጦርነትን እንድትደግፍ በዝምታ አፏን ሸብቧታል። በፓለቲካ ምክንያት በተቀሰቀሰው ጦርነት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከጎንዎ እንድትቆም አስገድደዋታል። ቤተክርስቲያን ጦርነትን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ውላለች እንዲሁም የቤተክርስቲያን መሪዎች አስከ አሁን ድረስ ለአስራ አንድ ወራት ስለዘለቀው የሰብዓዊ ቀውስ እንዳይናገሩ ተከልክለዋል። 

ቄስ ጉዲና ቱምሳ አሁን በህይወት ቢኖሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ለፓለቲካ ጥቅምዎ ሲሉ በድለዋታል ይልዎት ነበር እንዲሁም እንደኔ ከስልጣን እንዲለቁ ይጠይቁ ነበር። 

2. የትግራይ ጦርነትና የሰብዓዊ ቀውስ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ወንጌላዊና ወንጌላዊ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን ልብ የገዛው የራስዎ ፍልስፍና መደመር ነው። መደመር አብሮነትን፣ወንድማማችነትንና አንድነትን የሚያደነቅ የግልና የቡድን ልዩነቶችንም የሚያከብር ውህደት እንደሆነ ገልጸዋል።የመደመር ፍልስፍናዎ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ የፍቅር ተምሳሌት ጋር በተለይም በጆሃኒን ሥነ-መለኮት ከተገለጸው ጋር የሚጣጣም ነበር።

ለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መርህ ላይ ለተመሰረተ መርህ ቁርጠኝነት ኦሮ-ማራ የተሰኘ ኢ-መደበኛ የሆነ ጥምረት እንዲፈጠር አበረታቱ። ይህን ማድረግዎ የኢትዮጵያን ሁለት ትልልቅ ብሔሮች አንድ ለማድረግ ሳይሆን አናሳውን ትግራይ ገሸሽ ለማረግና ለመቃረን አልመው ያደረጉት መሆኑ አሁን ግልጽ ነው። ይህ ኢ-መደበኛ የሆነ ጥምረት ከአብሮነት መርህ የወጣና ተጋሩዎችን የሚቃረን ስልታዊ ጥምረትን የሚወክል ነው ይህም ተጋሩዎች በአገሪቱ ግጭት አይቀሬ እንደሆነ እንዲጠረጥሩና እንዲጠብቁ አድርጓቸዋል። 

ምንም እንኳን የትግራይ መሪዎችም የስልጣን ጥመኞችና ለእርስዎ አመራርም ተቃራኒ የነበሩ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ቢሆንም በእርስዎና በህወሃት መካከል ያለውን ልዩነት ያስተናገዱበት መንገድ፤ እከተለዋለሁ ከሚሉት መርሆዎች ጋር የሚሄድ አልነበረም። ፍቅርን ከማስተዋወቅ ይልቅ ከበቀለኛ የውጭ ኃይል ጋር መተባበርን መረጡ። 

ለወራት ውጥረት ከነገሰ በኋላ የትግራይ መሪዎች የሰሜን እዝን በጥቅምት 24 2013 ዓ.ም በማጥቃት ጦርነቱን ጀመሩ። የትግራይ መሪዎች ይህን ያደረጉት ግጭት የሚጠበቅ በመሆኑና እራሳችንን ለመከላከል ነው ይላሉ። መንግስትዎ እስከ አሁን ድረስ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሰዎች ህይወት እያስገበረ ያለ ሙሉ ወታደራዊ እርምጃ ወሰደ። ለሰሜን እዝ መጠቃት የፌደራል ሰራዊቱ ምላሽ በሂፖ ቅዱስ ኦገስቲን ፍትሃዊ ጦርነት መላምት መሰረት ምናልባት ትክክል ቢሆንም በቀለኛ የሆነን ሃይል፤ወታደሮቿ ሊነገሩ የማይችሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በትግራይ ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የፈጸሙትን ኤርትራን መጋበዝ ከባድ ስህተት ነበር። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እርስዎ እያዩ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰራዊቶች እንዲሁም የአማራ ታጣቂዎች የተከናወኑ ሊነገሩ የማይችሉ ሰቆቃዎችን ተመልክተናል። ህወሃት ስልጣን ላይ ከነበረበት ከ1983 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም ድረስና ይህ ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ በትግራይ ኃይሎች የተፈጸሙ አረመኒያዊ ተግባራት በማንኛውም መንገድ በእርስዎ መንግስት ወታደሮች የትግራይ እናቶች መደፈራቸውን ልክ አያደርገውም። 

በንጽጽር ጥሩ ለመምሰል ምንም ያህል እራስዎን ከህወሃት ጋር ቢያነጻጽሩም በእርስዎ አዛዥነት ስር ባሉ ኃይሎችና በአጋሮችዎ የተፈጸሙ አረመኒያዊ ተግባራት ምክንያታዊ ሊሆኑ አይችሉም። ስለፍቅር ቢናገሩም ከህወሃትና ከሌሎች የፓለቲካ ኃይሎች ጋር በመሆን በትግራይና በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል እንዲሁም በተጋሩዎችና በኤርትራውያኖች መካከል ጥላቻ ዘርተዋል። 

ይህ የስነምግባር አመራር ጉድለት በሌሎችም ወንጌላውያን ሊተች ይገባል። ለዚህም ነው እኔ ከስልጣንዎ እንዲለቁ የምጠይቀው። 

 3. እየጠበበ የመጣው የፓለቲካ ሜዳና የአመጽ/ሁከት አዙሪት

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ2011 ዓ.ም ካደረጉት መልካም ነገሮች በሙሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው የፓለቲካ እስረኞችንና የህሊና እስረኞችን ከእስር መልቀቅዎ ነው። ያለአግባባ የታሰሩትን ነፃ እንድንለቅ ያስተማረን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ሉቃስ 4፡18)።

ይህን መሲሐዊ ኃላፊነት በመውሰድ የህሊና እስረኞችን ነፃ ለማውጣት በሙሉ ታዛዥነት ሰርተዋል። በከፊል በእርስዎ እንቅስቃሴ የተነሳ 40,000 እስረኞች ከእስር ተለቀዋል። እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉ የፓለቲካ እስረኞች በዋነኝነት በእርስዎ አማካይነት ከተፈቱ እውቅ የፓለቲካ እስረኞች መካከል ይገኙበታል። 

ነግር ግን ይህ ነፃነት ዘላቂ አልነበረም። የእርስዎ አምባገነናዊ ጎኖች የመደመር እሴቶች ላይ የበላይነት እየያዙ ሲመጡ እስር ቤቶች በደካማ ማስረጃ በተወነጀሉ እና ምናልባትም ጥፋታቸው እርስዎን መቃወም ብቻ በሆኑ እስረኞች መሞላት ጀመሩ። ይህ በተለይም ከተወዳጁ የኦሮሞ ሙዚቀኛ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ግልጽ ሆነ። በኦሮሚያ ያሉ በርካታ እስር ቤቶች በኦሮሚያ ፓሊስ በጅምላ ከጎዳናዎች ላይ ተይዘው በቁጥጥር ስር በዋሉ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከአፍ እስከ ገደፍ ሞሉ። የተወሰኑ ወንጌላውያንና የቤተክርስቲያን መሪዎችም በቁጥጥር ውስጥ ውለው ነበር ይህም የሆነው በሃጫሉ ግድያ ጊዜ በመንገድ ዳር ስለነበሩ ነው። 

ከሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት በኋላ በመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈ ከፍተኛ ስብሰባ ላይ የተናገሩት ነገር የስነምግባር አመራር ተደርጎ ከሚታሰበው የእርስዎ አመራር ጋር የተቃረነ ነው። በይፋ ‘’ምንም ያህል ሰው ቢሞት’’ ማንም የእርስዎን ስልጣን እንደማይነቀንቅ አወጁ። ከዛም በጣም አጠያያቂ የሆነ ንግግር በማድረግ ‘’ለመዋጋት ከፈለጋችሁ፤በከተማም ሆነ በጫካ እናሳያችኋለን’’ አሉ። ተንኳሽ የሆነው ንግግርዎ በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ወደ ጫካ እንዲመለሱ አድርጓል። አሁን በኦሮሚያ ከዓመትና ሁለት ዓመት በፊት ከነበሩት የበለጠ አመፀኛ ቡድኖች አሉ። ይህ አሳዛኝ እውነታ ነው! 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስልጣንዎን ከመልቀቅ ሚሊየን ህይወቶችን መገበር እመርጣለሁ እስከማለት ደርሰዋል። ወጣቱ በከተማ ውስጥ ተቃውሞውን ከማሰማት ይልቅ ወደ ጫካ ሄዶ የትጥቅ ትግል እንዲያካሂድ በይፋ ጠቁመዋል። ይህ ኃላፊነት የጎደለው ጥቆማ አገሪቱን በሺህዎች የሚቆጠሩ ህይወቶችን አስገብሯታል። በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች የትጥቅ ትግል ተስፋፍቷል። ለምሳሌ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ሙሉ ለሙሉ ጦርነት ተፈጥሯል። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ወቅት ይቀበሏቸው/ይደግፏት የነበሯቸውን መርሆዎች ተከትለው መኖር አልቻሉም። ወጣቶች ከጫካ እንዲመለሱ ለማሳመን አልቻሉም። የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈውን የአመጽ/ሁከት አዙሪት ለማስቆም አልቻሉም። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ማድረግ የሚችሉት ከሁሉም የተሻለው ነገር ስልጣን መልቀቅ ነው።

4. ግጭቶችን ለመፍታት ሰላማዊ መፍትሄን መቃወም

የእግዚአብሔር ልጆች ባህሪ ሰላም ፈጣሪነት ነው። ክርስቶስ እንዳለው ‘’ሰላም ፈጣሪዎች የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና’’። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእርስዎን ሰላም ለመፍጠር ታዛዥ መሆንን ለጎረቤታችን ኤርትራ የእርቅ እጅ ሲዘረጉ አይተናል። የጥላቻን ግንብ አፍርሰው በሁለቱ አገራት መካከል የፍቅር ድልድይ ገንብተዋል። 

ሰላም ለማስፈን ላደረጉት ጥረት የኖቤል ኮሚቴ በ2012 ዓ.ም የሰላም ሽልማት ሸልሞዎታል። አሸንፈው በኦስሎ ንግግር ሲያደርጉ እንደ እርስዎ ሰላም ፈጣሪ አርገው እራሳቸውን የሚቆጥሩ የእግዚአብሔር ልጆች ፊት ላይ የፈጠሩትን ፈገግታ ለመግለጽ አልችልም። 

ምንም እንኳን ለእርስዎ ይህ ሽልማት ከፍተኛ ኃላፊነት ይዞ የመጣ ቢሆንም በርካታ ኢትዮጵያውያኖች ሽልማቱ በብሉይ ኪዳን ላይ ሰዎች መጠለያ ያገኙባትና ብቀላ የጠፋባት የስደተኞች ከተማ ጋር ተመሳሳይ ታሪካዊ ስኬትን እንደሚያመለክት አምነው ነበር። እንደ ሥነ-መለኮት መምህርነቴ ግን እርስዎ በዋነኝነት መታመን የነበረብዎት ለኖቤል ሽልማት ሳይሆን ለክርስቶስ ቃል እንደነበር አምኜ ነበር።

ከግምቶቼ በተቃራኒ ሰላምና እርቅ የሚሉት ቃላት በእርስዎና በመንግስትዎ አይነገሩም ወይም አይተገበሩም። በእርስዎ አስተዳደር ሰላም መፍጠር ተቃዋሚን መደገፍ ተደርጎ አዲስ ትርጉም ተሰጥቶታል። አገራዊ መግባባትን ማስተዋወቅ ስልጣንዎን መፈታተን ተደርጎ ተወስዷል። ሰላም መፍጠርን አሻፈረኝ ማለት በአንድ ወቅት እከተለዋለሁ ይሉት ከነበረው የስነምግባር አመራር ጋር አይሄድም። 

የኖቤል ሽልማትን የሰጡዎት ምዕራባውያን አገሮች እራሳቸው ለትግራይ ጦርነት የተኩስ አቁምና የፓለቲካ መፍትሔ ሲጠይቁ የሉዓላዊነትን ካርድ በመምዘዝ ከማንኛውም ‘ጠላት’ ጋር ውይይት ማድረግን አሻፈረኝ አሉ፤ ህወሃትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን አሸባሪ ቡድኖች ብለው እስከመሰየም ደረሱ። በዚህም ምክንያት አገሪቱ በቅርቡ የማያበቃ ምናልባትም የውክልና ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእግዚአብሔር ልጆችን የሰላም መፍጠር ሚና ገሸሽ አድርገዋል። ባስተማሩት የስነምግባር መርሆዎች ላይ ተመርኩዘው አጣብቂኝ ውስጥ ለገቡ በሚሊየን ለሚቆጠሩ ህይወቶች ሲሉ ፓለቲካዊ ፍላጎቶችዎንና ኃላፊነትዎን መስዋዕት ማድረግ ነበረብዎ። ያለእራስን አሳልፎ መስጠት መስዋዕትነት ምንም አይነት ሰላም አይመጣም። ትግራይና ኦሮሚያን ለማጥቃት ከኤርትራ ኃይሎች ጋር ከመተባበር እራስዎን ዝቅ በማድረግ በውይይት እና እርቅ ሰላም ለማምጣት መሞከር ነበረብዎ። ይህ አይነት መስዋእትነት በ2011 ዓ.ም ለኢሳያስ አፈወርቂ እጅዎትን በመዘርጋት ከኤርትራ ጋር ለ20 ዓመታት የነበረውን ፍጥጫ ከቋጩበት ጊዜ ጋር የሚመሳሰል ነው። 

ሰላም ፈጣሪ የመሆን ሚና ለመጫወት አሻፈረኝ ማለትዎና የኢትዮጵያን በርካታ ልዩነቶች ለማስታረቅ አለመቻልዎ በዚህ ሰዓት ከስልጣን መልቀቅዎ ለአገሪቱ ማድረግ ከሚችሉት ከሁሉም የተሻለ ነገር የሆነበት ሌላው ምክንያት ነው።

5. ፍቅር ከኤርትራ አገዛዝ ጋርና እየጨመሩ ያሉ አምባገነናዊ አዝማሚያዎች

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ምንም እንኳን ለእርስዎና ለአስተዳደርዎ ያለኝ ድጋፍ ስልጣን ላይ በወጡ በመጀመሪዎቹ አመት ከመንፈቅ ጊዜያት የማይናወጥ የነበረ ቢሆንም ሁልጊዜም የኤርትራው ፕሬዝደንትን እና ከእሳቸው ጋር ያለዎትን ግንኙነት ስከታተል ቆይቻለሁ። በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው እርቅ አድናቆታቸውን ቸረዋል/የተፈጠረውን እርቅ በደስታ ተቀብለዋል። እርቁ ለበርካታ የኤርትራ ወንድሞችና እህቶችም ብርሃንን ፈንጥቋል። ኤርትራውያኖች ጎረቤቶቻችን ሆነዋል፤ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞችም ኑሮ ለመመስረት ቀላል ሆኖ አግኝተውታል። አሁን በአዲስ አበባ የወንጌላዊ አምልኮ ዝግጅቶ ላይ የትግርኛና ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ቁጥር እኩል ሊሆን ምንም አልቀረውም። 

ኤርትራውያን ጎረቤቶቻችንና ጓደኞቻችን ኢትዮጵያን ስለሚወዱ ብቻ አይደለም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። ወደ ኢትዮጵያ ባይመጡ ኖሮ በሊቢያ አርገው ወደ አውሮፓ ያመሩ ለነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ኢትዮጵያ መጠለያም ስለሆነች ነው። ኤርትራውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ወደ ጣልያን ለማቋረጥ ሲሞክሩ በሜድትራኒያ ባህር የመስጠማቸውን ዜና  መስማት የተለመደ ነው። ይህንን መስዋዕትነት የሚከፍሉትና ኢትዮጵያን እንደ መጠለያ የሚመርጡት የኤርትራ መንግስት ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን እየጣሰ ስለሆነ ነው። 

ኢሳያስ አፈወርቂ ከሃያ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ሲደርሱ ‘’በኤርትራ የሚገኙ ወንጌላውያን እስረኞች ይፈቱ’’ የሚል መፈክር ይዤ ነበር ልቀበላቸው የሄድኩት። የኢሳያስ አስተዳደር በርካታ ሰባኪዎችን አስሯል እንዲሁም አሰቃይቷል በተጨማሪም ጴንጤቆስጥያዊ በአገሪቱ በህግ አግዷል።ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጴንጤቆስጤ  ኤርትራዊ ቢሆኑ ከረዥም ጊዜያት በፊት ታስረው ነበር። ጴንጤስቆጥያውያን ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ሙስሊምና ኦርቶዶክስ የሥነ-መለኮት መሪዎች አምባገነንነትን ተቃውመው በመናገራቸው በኤርትራ ታስረው ይገኛሉ። 

ሆኖም ግን ለአምባገነኑ አላስፈላጊ የሆኑ የፍትህን ዋጋ በሚያሳንሱ ይፋ በሆኑ ድርጊቶች የታጀበ የሞቀ አቀባበል ነው ያደረጉላቸው። በፍጥነት በሁለታችሁ መካከል እየተካሄደ ያለው ነገር እውነትም ፍቅር እንዳልሆነ ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጋራ የብቀላ ፍላጎት እንደሆነ ግልጽ ሆነ። በይፋ ኤርትራ ዲሞክራሲ አያስፈልጋትም ብለው ያወጁትን ኢሳያስን ባህሪ ይቀይራሉ ብለን ስንጠብቅ እርስዎ በምትኩ አምባገነናዊ ተግባሮቻቸውን መከተል ጀመሩ። 

ከኢሳያስ በተለየ መልኩ እርስዎ ቤተክርስቲያናትን አልዘጉም ከእሱ ይልቅ አጋሮችዎ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ተቋማቶቻቸውን ተቆጣጥረዋል። ከኢሳያስ በተለየ መልኩ እርስዎ ‘’ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አይስፈልጋትም’’ ብለው በይፋ አይናገሩም ነገር ግን ምርጫውን ፓለቲከኞችን በማሰርና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ገሸሸ በማድረግ ያለ ተፎካካሪ ማለት ይቻላል ተወዳደሩ። በዚህም የተነሳ ፓርቲዎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 96 በመቶ መቀመጫዎችን እሸንፌያለሁ ማለት ችሏል። እንደ ኢሳያስ በማይተችዎትና ሊተችዎች በማይችሉ ሰዎች እራስዎን ከበዋል። 

እኔ ሁልጊዜም የኤርትራ አምባገነናዊ ስርዓትን ስቃወም ኖሬያለሁ። ጊዜው ሲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእርስዎንም ስርዓት እንደምቃወም ገምቼ ነበር። አሁን የነብይነት ድምጽ እንዳለው የሥነ-መለኮት  መምህር በእርስዎ አምባገነናዊ ድርጊቶች የተነሳ ዝም አልልም ፤አልፈራም። ስለዚህ የእርስዎን ከስልጣን መነሳት እጠይቃለሁ። 

6. እየጠፋ ያለ ተጠያቂነትና እውነትን በሚመች መልኩ ማበጀት (እውነትን እንዳሻ ማድረግ)

በአስተዳደርዎ ላይ ተስፋ እንድቆርጥና ስልጣንዎን እንዲለቁ እንድጠይቅዎ ካደረጉኝ በርካታ ተግባራት እጅግ ከባዱ እውነትን የሚበድሉ መሆንዎ ነው። ብዙ ጊዜ በፓለቲካ ውስጥ እውነት ርካሽ ሸቀጥ ናት ይባላል። በኢትዮጵያ የሥነ-መለኮት መሰባሰቢያዎች ውስጥ ግን እውነት እንደዛ አትታይም። እውነት በእግዚአብሔር በሁሉም ስፍራና ከሁሉም የበላይ በሆኑ የስነምግባር ህጎች የሚገለጽ ፍጹም የሆነ አካል ነው። 

በኢትዮጵያ ያሉ በርካታ የሥነ-መለኮት መሪዎች አስተዳደርዎ እውነትን እንደ ርካሽ የሚሸጥ የሚለወጥ ሸቀጥ ከመመልከት ይልቅ በጥብቅ የስነምግባር መሆዎች ላይ የተመረኮዘ እውነትን ከፍ ባለ ደረጃ  ይዞ እንደሚቆይ አምነው ነበር። ደጋግመው ‘’እውነት ከኛ ጋር/ጎን ናት’’ ሲሉ የጠበቅነው ነገር ይህንን ነው። ከጠበቅነው በተቃራኒው በአስተዳደርዎ እውነት (የፕሮቴስታንት ተሃድሶ አባት የሆነውን የማርቲን ሉተርን ቃል ለመጠቀም) እንደ ሴተኛ አዳሪ ነው የተቆጠረችው። 

እርስዎና አስተዳደርዎ ለመገናኛ ብዙሃን የተናገሯቸውን ውሸቶች በሙሉ መቁጠር አዳጋች ነው። የተወሰኑት ነገሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀይሩ ውሸቶች (በተለይም በእርስዎ የተነገሩት ውሸቶች) እከተለዋለሁ ብለው በግልጽ ያወጁትን የስነምግባር አመራር የሚጎዱና የሚቃረኑ ናቸው። በተለይም የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ ጣልቃ እንዳልገቡ ለበርካታ ወራት ሲናገሩ መቆየትዎ፣መጀመሪያ አካባቢ በጦርነቱ ማንም ሰላማዊ ሰው ትግራይ ውስጥ እንዳልተጎዳ መናገርዎ፣በቅርቡም በትግራይ ምንም ረሃብ እንደሌለ መሟገትዎ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በብሔራዊ ምርጫው እንዲሳተፉ መለመንዎን ነገር ግን እነሱ አሻፈረኝ ማለታቸው ይጠቀሳሉ። 

እነዚህ ንግግሮች ብቻ አስተዳደርዎ ምን ያህል በእውነት ላይ ተመርኩዞ ለመስራት እንዳልቻለ አረጋግጦልኛል። እንደዚህ ያሉ ንግግሮች ውሸትዎ የህዝብን አፍ በዝምታ ማሸበብ እስከቻለ ደረስ ንግግሮችዎ እውነት ይሁኑ አይሁኑ ግድ እንደማይሰጥዎት እንዳምን አድርገውኛል። 

ይህ እውነትን የሚያዩበት መንገድ እውነት ነፃ ያወጣል (ዮሀንስ 8፡32?) እንዲሁም እውነት ክርስቶስ ነው (ዮሀንስ 14፡6?) የሚለውን የእውነትን ትርጉም ያሳንሳል። እውነት ህብረተሰብን ነፃ ሲያወጣ ውሸት ግን ያሽመደምደዋል። ሰይጣን የውሸት ሁሉ አባት ነው ክርስቶስ ደግሞ እውነት ነው። ምንም እንኳን የስራ ጫናዎ ብዙ ጊዜ እንዲዋሹ ቢያስገድድዎትም እውነትን እርስዎ እንዳሻዎት የሚያደርጉት ርካሽ ሸቀጥ ማረግ የለብዎትም። 

ውሸት ማንንም ነፃ አያወጣም። ውሸት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። የሚያመጣ ከመሰለዎትና መዋሸት ከቀጠሉ መጨረሻዎትን ሊሆን ከሚችለው የበለጠ የከፋ ያደርጉታል። ስለዚህ የተሻለው ነገር እውነተኛ መሆንና ሃይማኖታዊ እምነትዎችን/መርሆዎችን መከተል ነው። በእርስዎ የስነምግባር አመራር መውደቅ የተነሳ በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፤በርካቶችም ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ለዚህም ነው ስልጣንዎን እንዲለቁ የምጠይቅዎ። 

በስተመጨረሻም ይህ ፤የስነምግባር ግዴታዎቹ የመገናኛ ብዙሃን ከሚሉት ነገሮች የበለጠ ጠንካራ ሆኖ ካገኘው በክርስቶስ ወንድምዎ ከሆነ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ነው። አብያትክርስቲያናትና መስጊዶች ወይም የምክር ቤት አባላቶችዎ በስነምግባር አመራር መውደቅዎን አይነግሩዎትም። የሥነ-መለኮት መምህር ተግባር ልክ እኔ እዚህ እያደረግኩት እንዳለሁት የነብይነት ድምጽ መሆን ሲሆን ከዚህ ግጭት መውጫ መንገድ መፈለግ ግን የፓለቲከኞች ድርሻ ነው። ስለዚህ በዚህ ሰዓት ማድረግ የሚችሉት ከሁሉም የተሻለው ነገር በክብር ከስልጣንዎ መውረድ ነው ይህንንም በማድረግዎ ለተኩስ አቁምና ለብሔራዊ ውይይት በር ይከፍታሉ። 

 

ከሰላምታ ጋር 

ናዖል  በፍቃዱ

Query or correction? Email us

Follow Ethiopia Insight

This is the viewpoint of the author. However, Ethiopia Insight will correct clear factual errors.

Main Photo: Abiy giving speech at the inauguration of his book ‘Medemer’, PMO, 20 October 2020.

Join our Telegram channel

Published under Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International licence. Cite Ethiopia Insight and link to this page if republished.

We need your support to analyze news from across Ethiopia
Please help fund Ethiopia Insight’s coverage
Become a patron at Patreon!

About the author

Naol Befkadu

Naol is a theologian and medical doctor who is pursuing his PhD in Leadership from Vision International University. He has authored several books, most recently ‘Yaanni Koo: A Reflection on Aspects and Attitudes towards Love; the Ethiopian Context’. Follow him on Twitter @DrNaolBK

15 Comments

 • ??????????????????????????Whatever pm Abiye done well done
  U are full of jealous
  Ethiopia in this moment don’t have any one . Better than DEAR PM ABIYE
  We wish pm lead as much as he can for better Ethiopia????????????????????????????????????

 • Shame on today’s Christianity. Shame on you. Because you don’t know God you depend on your fleshy mind to act like as if you were sent by God. You are not Christian.

 • አቶ ናኦል በጽሁፍዎ መጀመሪያ መንፈሳዊ ኒሻንዎን ሲደረድሩ አንዳች መልካም ነገር አላጣብዎትም ብዬ ጽሁፍዎን ተከትዬ ቁልቁል ብወርድም የሚረባ ነገር አይደለም ጭራሽ ሥጋ ሥጋ ሸተተኝ፡፡ሰለዚህ ጽሁፍዎን አልጨረስኩትም፡፡ አንድ ነገር ግን ልንገርዎ፡፡ በቅርቡ በተደረገው ሕዝባዊ ምርጫ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለማያውቃቸው የብልጽግና እጩዎች ድምፁን የሰጠው አቢይን ስለወደደ ነው፡፡ ሕዝብ አቢይን የወደደው በቁመናው ሳይሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት በሰራው ስራ ነው፡፡ ግን ግን ሕዝብ የመረጠው አዲስ መንግሥት ስራ በጀመረ ማግስት ጠቅላዩ ስልጣን እንዲለቁ መጠየቅዎ ምን አስበው ነው ? ብቻ ለሆነ ሴራ የመንፈሳዊ ካባ ተጠቅመው ከሆነ እግዚአብሔር የእጅዎን አይንፈግዎ፡፡

 • የተከበሩ አቶ ናኦል፣ አስቀድሜ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። ከዚያ አስተያየቴን በቅደም ተከተል ላስቀምጥ
  1. ሲጀመር ዶ/ር አብይ የወንጌል አማኝ እንጂ ወንጌላዊ አይደሉም፣ እርሶም ይመስሉኛል።
  2. የስነመለኮት ትምህርት እንዳሉት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ስላለው ግኑኝነት የሚያጠና ሳይንስ ነው፣ ይህንን እዚህ ላይ ማንሳት አስፈላጊ አልነበረም።
  3. ዶ/ር አብይ “አድናቆት በተቸረው ሁኔታ” ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ለእርሶ መንገር አይጠበቅብኝም።
  4. የካውንስሉን መመስረት መደገፍ መብትዎ ነው፣ እንድዚሁ ሁሉ የካውንስሉ መሪ ፖለቲከኛ መሆንም መብታቸው ነው። ዶ/ር አብይ እዚህ ላይ ምን ተሳትፎ ኖሯቸው ነው ስልጣን እንዲለቅቁ መጠየቂያ ምክኒያት ያደረጉት። ሰውየው`ኮ በፊትም አባል ቢሆኑ ነው ለምርጫ ሊወዳደሩ የቻሉት። እንደሚያውቁት የፓርቲው አባል የሆነ ሁሉ ለምርጫ አይወዳደርም።
  5. ሁለተኛው ነጥብዎ ግን የፖለቲካ አቋሞን እንድጠይቅ የሚገፋፋ ነው። የኤርትራ መንግሥት ተጠይቆ ሳይሆን ተገድዶ ነው የገባው፣ ምነው አስመራ በሮኬት ስትደበደብ የት ነበሩ? ሌባ በሮን ሲቆረቁር ዝም ብለው ነው ወይ የሚጠብቁት? ሌላው ከአንድ የስነመለኮት መምህር የማይጠበቅ ነገር መናገርዎ ነው – አሉባልታ። በትግራይ እናቶች ላይ ደረሰ ስላሉት ጉዳት ምን ማስረጃ አሎት? የመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካዮች ያሉትን አልሰሙም? አሉባልታ መልካም አይደለም!
  6. ስለፖለቲካው ሜዳ እኔና እርስዎ ሳይሆኑ ፖለቲከኞቹ ይናገሩ፣ በእርስዎ በተለይ አያምርም። ሜዳው ጠበበ ሲሉ “እነ ጃዋር ለምን ታሰሩ?” ማለት ፈልገው ከሆነ ፍ/ቤት ሄደው ይጠይቁ። የስነ መለኮት መምህር ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅበት ነበር።
  7. አሸባሪ ተብለው ስለተሰየሙ ቡድኖች ‘አሸባሪ’ ያላቸውን ወገን ለምን አልክ ብለው ይጠይቁ፣ ‘አላዋቂ ሳሚ . . . ” ከመሆን ይጠበቁ ነበር። ለሰላም የተሄድበትንም ርቀት እንደዚሁ ጠይቀው ይረዱ እንጂ በአሉባልተኞች ወሬ አይነዱ።
  8. “ቢቻላችሁስ ከሰዎች ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ” የሚለውን የጌታ ቃል ይዘነጉታል ብዬ አላስብም። ኤርትራ ውስጥ ያለውን ትክክል ያልሆነ ነገር እስኪታረም መጠበቅ ነው የሚሻለው ወይስ በጎ ተጽዕኖ ማሳረፍና መመለስ? ባለፉት 12 ወራት ስለተፈቱት የወንጌል አማኞችስ ሰምተዋል? በቂ ባይሆንም ጅማሮ አለ ለማለት ነው። አስትውሉ!!
  9. አዋቂ ነኝ የሚል በበዛበት አለም ስለምንኖር ስለ “እውነት” ያነሱት ነጥብ ግን ረከሰብኝ። እውነት ምንድን ነው? እውነት መናገርና እውነት ልዩነት አላቸው፣ ይልቁንስ የተናገሩት ሃሰት ነገር ካለ እሱኑ መሞገት እንጅጂ’ሴተኛ አዳሪነት’ን ምን አመጣው?
  በእድሜ ሳይሆን በትምህርት ደረጃ ታናሽዎ ከሆንኩት ከእኔ ጥቂት ምክር ብለግስ የፈቀድልኝ። “ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና” መክ. 5:1 እንደሚል ለመፃፍ ከመጀመርዎ በፊት ነገሮችን በጥንቃቄ ቢፈትሹ መልካም ይሆን ነበር። “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው” መክ. 3:7

  • አቶ ተፈራ፣ በአጭሩ ለኚህ ለተሳሳቱ እና ምናልባትም ለተገዙና ቅናት ላናወጣቸው ሰው በጣም የተስተካከለ መልስ ስለሰጡ በጣም አድርጌ አመሰግኖታለሁ። ፀሀፊው በጣም የተዛባና እራሳቸውን በጣም ከፍ አርገው ይናገራሉ። ምን ያህል ዝቅ እንዳሉ ግን የገባቸው አይመስልም። አፍሪካን ያታለ ለዋት የዚህ ፀሀፊ አይነቶች ናቸው።ኢትዮጵያ አንድ አገር ወዳድ መሪ ብታገኝ ምቀኞች በዙባት። በነገራችን ላይ አብይ አህመድ ቢነሱ በምንም ዘዴ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሽብርተኞች ጋር ስምምነት አያደርግም። ይህ የመሪ ጉዳይ አይደለም። የህልውና ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ያወቁት አይመስለኝም።

  • ተፈራ ሆይ እግዚአብሔር ይባርክዎት። ናኦድ ለተባሉት ሰው ስለ ዶ/ር አብይ ስልጣን ለፃፉት ፅሁፍ መልስ ለመመለስ አሰቤ ጨርሼ ለማንበብ ስወርድ የእርስዎን መልስ አገኘሁና እርፍ አልኩ፤ ምክንያቴም በትእግስት የመመለስ ኃይል ስለሚጎለኝ፤ እርስዎ ግን መልካም ትዕግስትና ሐሳብዎን በቅደም ተከተል ፍሰቱን ጠብቆ እንዲሔድ ማድረግ ስለሚችሉ እኔንም የሚወክል መልስ ስለሰጡልኝ ወደፊትም በዶ/ር አብይ ጉዳይ ይናገሩልኝ እኔ አድመጭዎ ነኝ፤ አክባሪዎ ነኝ።

 • Whatever Dr Abiy has done or trying to do has been interpreted differently by you. You even called Lema Megersa being sidelined etc, which you may not know the reason behind. We Ethiopians love Dr Abiy’s leadership. In a country where there are so many problems, this is the leadership that can bring us out of it. A God fearing person, who has demonstrated by action what he promised. Trying to link him with Church problems is unfair. You will not deny that he has been democratically elected to be the Prime Minister. So it says it all. If you yourself is a believer, don’t get involved in politics instead do something good for country.

  • It is always good to respond and react to a thesis. However, the public needs a genuine, purposeful and intellectual rebuttal, not a cadre-level, superficial and lame reasoning. The post made a rare and brave, and even graceful critique of Abiy Ahmed’s political leadership. Please tell us what Ethiopia got out of Abiy Ahmed’s leadership during the last three years.

 • Wendimee Naol selam lanteena endantee ayinet hasabi lemiketeluna lemiyaramidut huluu yihunilign. Silitan ke talakuu ke Egiziabiher kalihoone lemanimi ayisetimina komi bilehii asibibeti. YeSaol betii eyedekeme yeDawit betii eyebereta hedee yemilewun kali degimee lasasibih. Kiburi Dr Abiyi Ahimed Wuduu meriyachinini yemeretinewu egnaa silezihi wededikim telahim lemiketilut ametati egnamii anteem enigezaletalen. Yiliki Bahir madoo honehii kemititsifi tega belinaa hasabi lemesiteti bitimokiri yishalali. Degimoo yemeretinewu ekoo egnaa rasachini aniten mini asichenekehi? Bekaa enigezaletalen kuritihin ewek.

 • I found your proposal biased by hiden political motive.being theologian can’t necesserily enable you make political analysis. knowing boundary of knowledge is being wise.insisting the resignation of elected by people PM is shameful.

  • This idea is of great arogancy illiteracy & disobeying law.this is punshable by human law &by God.shame to talk about force.

Leave a Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.